ስለ እኛ

የነፍሰ ኄር መጋቤ ምሥጢር መሠረት ተሰማ ደቀ መዛሙርት የመሰረቱት

ዳረጎት ከራት በኋላ እንደጭማሪ፣ እንደማጠንከርያ የሚቀመስ ቀለል ያለ መብል ነው፡፡ እናንተም ዋናውን መንፈሳዊ መብል ከሊቃውንት አባቶቻችን አንደበት፣ ከመጻሕፍት ምስክርነት፣ ከደጋግ አበው ሕይወት፣ ከቤ/ክ ተጋድሎዋና ድሏ እየተማራችሁ ይህችን የኛን ዳረጎት ቅመሱልን፡፡

ተልኳችን

ዳረጎት ዘተዋሕዶ ለትርፍ ያልተቋቋመ (non-profit) በተለያዩ ቋንቋዎች የሚታተም የድረ-ገጽ መጽሔት (online magazine) ነው፡፡ ዳረጎት ነገድ፣ ቋንቋ፣ ዘር ፣ዕድሜ፣ ወንድ፣ ሴት ሳይልመጽሐፍ ቅዱስን መሰረት አድርጋ የምታስተምረውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ዶግማዋን፣ ቀኖናዋን እንዲሁም ትዉፊቷን በሚገባ ያትታል፡ ፡መጽሔታችን ዘመነ አብርሖትን/Enlightment/ ለማምጣት የሚሰራ ሲሆን፤ አንባቢያንም ዶግማ (መሠረተ እምነትን) የመሳሰሉትንእውቀቶችን ከመጨመር ባሻገር በመንፈሳዊ ህይወታችን ሥር ሰደን የምንታነጽበትን ትምህርቶች ያደርሳል፡፡ ስለክርስቶስ ምስጢር እንድንናገር እግዚአብሔር የቃሉን ደጅ ይከፍትልን ዘንድ ጸልዩልን፡