አምዶች

  • ዝክረ መጋቤ ምሥጢር አለቃ መሰረት ተሰማ

    የዝክረ መጋቤ ምሥጢር አለቃ መሰረት ተሰማ ልዩ መንፈሳዊ ጉባኤ በዕለተ መድኀኔዓለም በልዩ ልዩ መርኃግብራት ሲከናወን ቆይቶ ማምሻውን ተጠናቋል። ወረብ፤ ትርዒቶች ዝማሬዎችና በእሳቸው ህይወት ላይ ያተኮረ አውደርእይ ተካሂዷል። ዳረጎት ሚዲያም ለዚህ ጉባኤ መሳካት የየድርሻቸውን የተወጡትን በሙሉ ማመስገን ይወዳል።


  • አለቃ መሠረት

    ”አለቃ መሠረት” የተሰኘውና የታላቁን አባት መጋቤ ምሥጢር መሠረት ተሰማን የሕይወት ታሪክ፤ የጿፏቸውን የሥነ-ጹሑፍ ሥራዎች፤ የተደረሱላቸውን ቅኔያት፤ የልጆቻቸውን ምስክርነትን የያዘው መጽሔት ቅዳሜ 26/10/2013 በአሰላ ደብረ መድኃኒት መድኀኔዓለም ቤተክርስቲያን ቤተሰቦቻቸው በተገኙበት በተዘጋጀው ትልቅ ጉባኤ ላይ በይፋ ተመርቋል። በዕለቱ ከዳረጎት ሚዲያ ለቤተሰቦቻቸው የልዩ ዕትሙ የፊት ገጽ በማስታወሻነት ተበርክቷል።