ዳረጎት ከራት በኋላ እንደ ጭማሪ ፣ እንደ ማጠንከርያ የሚቀመስ ቀለል ያለ መብል ነው፡፡ እናንተም ዋናውን መንፈሳዊ መብል ከሊቃውንት አባቶቻችን አንደበት፣ ከመጻሕፍት ምስክርነት፣ ከደጋግ አበው ሕይወት፣ ከቤ/ክ ተጋድሎዋና ድሏ እየተማራችሁ ይህችን የኛን ዳረጎት ቅመሱልን፡፡
ዳረጎት ዘተዋሕዶ ለትርፍ ያልተቋቋመ(nonprofit) በተለያዩ ቋንቋዎች የሚታተም የድረ-ገጽ መጽሔት(online magazine) ነው፡፡ ዳረጎት ነገድ፣ ቋንቋ፣ ዘር ፣ዕድሜ፣ ወንድ፣ ሴት ሳይል መጽሐፍ ቅዱስን መሰረት አድርጋ የምታስተምረውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ዶግማዋን፣ ቀኖናዋን እንዲሁም ትዉፊቷን በሚገባ ያትታል፡፡ መጽሔታችን ዘመነ አብርሖትን/Enlightment/ ለማምጣት የሚሰራ ሲሆን፤ አንባቢያንም ዶግማ(መሠረተ እምነትን) የመሳሰሉትን እውቀቶችን ከመጨመር ባሻገር በመንፈሳዊ ህይወታችን ሥር ሰደን የምንታነጽበትን ትምህርቶች ያደርሳል፡፡ ስለክርስቶስ ምስጢር እንድንናገር እግዚአብሔር የቃሉን ደጅ ይከፍትልን ዘንድ ጸልዩልን፡፡